ሐረር በሮቿ አምስት ናቸው። ዋናዎቹ በሮቿ ግን ሁለት ናቸው። የምስራቁ በር “ጌይ ጁገል” ማለት (የሐረር በር ) ሲባል የምዕራቡ በር ደግሞ “ጌይ ፈጋይ” ነው የሚባለው። የከተማዋ ዳርቻ እንደ ማለት ነው። በሁለቱም በር ዙሪያዎች ገብያዎች አሉ። እነሱም በሐረር በር ያለው “አደሬ ጉዶ” (ትልቁ አደሬ) ሲባል በ “ጌይ ፈጋይ” ደግሞ “አደሬ ጢቆ” (ትንሿ አደሬ) ይባላል። ጀጎል ግንብ የተገነባው በመካከለኛው ዘመን ነው። 5 ሜትር ከፍታ እና 3.5 ኪ.ሜ ርዝመት የለው ነው። በዙሪያውም ሽዋ በር ፣ ቡዳ በር ፣ ኤረር በር ፣ ሰንጋ በር እና ፋላና በር የሚባሉ በሮች አሉ። ዛሬ ላይ ሁሉም ሰው የሚያውቀው ሐረር በር የሚለው 1889 ዓ.ም የሐረር መስፍን ራስ መኮንን ያሠሩት ነው። እሱን ከጨመርን ሐረር ስድስት በሮች አሏት እንላለን። አምስቱን በሮች እነሆ
ቡዳ በር
ኤረር በር
ሰንጋ በር
ፋላና በር





አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ