#ደሴ
" አሞራ አይደለሁ ፥ ወይ ሳቢሳ፣
ላባይ ለጣና ፥ የምሣሣ፣
ከሐይቁ ዳር ፥ ቆሜ ቢያየኝ፣
እኔን #ደሴት አለኝ! " ብላ እርሷን #ደሴ ብላ ጠርታለች። ከዛ በፊት ግን ላኮመልዛ ትባል ነበር።
በሰሜን በሽሎ ወንዝ፣ በደቡብ ጃማ ወንዝ፣ በምእራብ አባይ ፥ በምስራቅ የአፋር ክልል የሚዋስኗት #ደሴ ከ1700 ዓ.ም በፊት #የቤተ_አማራ ግዛት ዋና ማዕከል ነበረች። ዛሬ ላይ #ቤተ_አማራ የኦሮሞ መስፋፋትን ተከትሎ #ወሎ ተብሏል። በዘመነ መሥፍንት ጊዜ
" የሸዋ ፣ የጎዣም ፥ ተበትኖ ከብቱ፣
የወሎ ፣ የትግሬ ፥ ተበትኖ ከብቱ፣
ገዛው አባ ታጠቅ ፥ ሰብስቦ በሀብቱ! " እንዲል ከአራቱ ግዛቶች አንዱ አንደ ነበር እና የዘመናዊት ኢትዮጵያ መሥራች ቴዎድሮስ ተቀምጦባት እንደ ነበር ታሪክ ያወሳል።
የወሎ ወይም የቤተ አማራ ድንበር በየዘመኑ የመስፋት እና የመጥበብ ሁኔታዎች የታዩበት ሲሆን በአንዳንድ የታሪክ አጋጣሚዎች እስከ አሰብ ድረስ ሰፍቷል። ከጣልያን ወረራ በውኃላም ማለትም በ1933 ዓ.ም አዘቦ፣ ላስታ፣ ራያ፣ ዋግ እና የጁ ይፋዊ የወሎ ግዛቶች ሁነዋል። ወሎ እጅግ ሰፊ የሚባል ጠቅላይ ግዛት የነበረው ሲሆን በስፋቱም ከሀረርጌ፣ ከባሌ እና ከሲዳሞ በመቀጠል በአራተኛ ደረጃ ላይ ነው።
coming soon full video

አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ