ኢትዮጵያ የባህር መዳረሻ ለማግኘት የምታደርገው ትግል በጂኦሎጂያዊ እንቅፋት፣ በታሪካዊ ውድቀት እና በከፍተኛ የጂኦፖለቲካዊ ውጥረት የታጠረ ነው። ነገርን ከስሩ፥ ውኃን ከጥሩ ነው እና እንዬው። ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ውስጥ ካሉት ዋና ዋና ሀገሮች አንዷ ብትሆንም፣ ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ ያለባህር በር መቆየቷ አገራዊ ደህንነቷን እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገቷን የሚገዳደር የዘመናት ችግር ሆኖ ቆይቷል። ይህ ታሪካዊ ፈተና፣ የጂኦሎጂያዊ ፍጥረት ሚስጥር ከሆነው #ከዳልሆል_ሳዶን ተፋሰስ እና ከአሁኑ የቀይ ባህር የኃይል ሚዛን ጋር የተሳሰረ ነው። በዳልሆል_ሳዶን ዙሪያ የኢትዮጵያ የባህር ኃይል ታሪክ የተጀመረው በንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ሲሆን፣ በ1955 ዓ.ም. ነው። በ1991 ዓ.ም. ወደ 11,500 የሚጠጉ ሠራተኞች እና 81 የሚደርሱ የተለያዩ ዓይነት መርከቦች የነበሩት ሲሆን፣ በጊዜው በአፍሪካ ውስጥ ካሉት ጠንካራ የባህር ኃይሎች አንዱ ነው። ኃይለ ሥላሴ የኢትዮጵያ የባህር ኃይል ዩኒፎርም ለብሰው። ዋና መሥሪያ ቤቱና ዋና የሥልጠና ማዕከሉ ምጽዋ ውስጥ የነበረ ሲሆን፣ ሌሎች መሠረቶቹ ደግሞ #አሰብ፣ #ዳህላክ_ደሴቶች እና #አስመራ ውስጥ ነበሩ። በ1996 ዓ.ም. ኤርትራ ነፃነቷን ስትቀዳጅ፣ ኢትዮጵያ ወደብ አልባ በመሆኗ የባህር ኃይሉ ተበተነ። መርከቦቹ በጅቡቲ እና በየመን ወደቦች ለጊዜው ከቆዩ በኋላ ተሸጡ። ፈረራሱ። ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያ ከ95% በላይ የንግድ እንቅስቃሴዋን በጅቡቲ ወደብ ላይ እንድታደርግ ተገደደች። የኢትዮጵያ ወደብ አልባነት መንስኤ የፖለቲካዊ ውሳኔ ቢሆንም፣ የቀይ ባህር ውኃ ወደ ዳንኪል በረሃ እንዳይፈስ የሚከለክለው ጂኦሎጂያዊ ምክንያት ደግሞ የ...
ግሎባል ኢንሳይት ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ጉዳዮች፣ በአፍሪካ እድገቶች እና በኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ ሰፊ፣ ጥልቅ ትንታኔ የሚሰጥ ዲጂታል ሚዲያ መድረክ ነው። በአለም አቀፍ ክስተቶች እና በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ላይ ያላቸውን ተፅእኖ ለማጣጣም በማለም ልዩ የአለም አቀፍ እይታ እና የሀገር ውስጥ እውቀት ውህደት ያቀርባል። መድረኩ ወደ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ አዝማሚያዎች ዘልቆ በመግባት የባለሙያዎችን አስተያየት፣ በመረጃ የተደገፈ ግንዛቤን እና ታሳቢ ትንታኔዎችን በማቅረብ ተመልካቾች የአለምአቀፍ እና ክልላዊ ተለዋዋጭ እንቅስቃሴዎችን ትስስር እንዲገነዘቡ ይረዳል።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ